የሕግ የበላይነት፡- ጽንሰ ሐሳቡ፣ መገለጫዎቹና የማረጋገጫ መንገዶች

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እውን እንድትሆን ለማገዝ ‹‹የሕግ የበላይነት፡- ጽንሰ ሐሳቡ፣ መገለጫዎቹና የማረጋገጫ መንገዶች›› በተሰኘ ርዕስ ቅዳሜ ግንቦት 10/2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 - 7፡00 ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒቴሽናል ኮሌጅ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ) የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ፣ የሕግ የበላይነት ጽንሰ ሐሳብ፣ ከዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ጋር ያለው ቁርኝት፤ የሕግ የበላይነት ማረጋገጫ መንገዶችና ተቋማዊ መሠረቶቹ፣ እንዲሁም የሕግ የበላይነትን በኢትዮጵያ ለማረጋገጥ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ጠቋሚ ጥናቶች በዘርፉ ምሁራን ይቀርባሉ፡፡ በጥናቶቹ የሕግ የበላይነት ተቋማዊ መሠረቶች፣ በተለይ ተጠያቂነትና ዴሞክራሲያዊ አሠራር፣ ፍትኃዊ የሥልጣን ክፍፍል፣ ተቋማዊ ቁጥጥር፣ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን እና የሲቪክ ማኅበራት ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ስለሚኖራቸው ሚና ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ይደረጋል፡፡

በውይይቱ፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የፍትሕ ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን አካላት፣ ተመራማሪዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እንዲሁም ኅብረተሰቡ ይሳተፋሉ፡፡ ስለሆነም እርስዎ በውይይቱ ላይ በመገኘት ውይይቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩልዎን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ በማክበር ጋብዘናል፡፡

ቅዳሜ ግንቦት 10/2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 - 7፡00 ሰዓት ድረስ

ቦታ፡- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒቴሽናል ኮሌጅ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ)

ሁላችሁም በውይይቱ እንድትሳተፉ በክብር ተጋብዛችኋል!

Date
End Date
Location
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒቴሽናል ኮሌጅ አዳራሽ (4 ኪሎ ግቢ)