የ‹The Great African Caravan> ቡድን በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

‹ዘግሬት አፍሪካን ካራቫን› የተሰኘው ቡድን ከተመሰረተ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ዓላማው በአስር አፍሪካ ሀገራት በመዘዋወር፣ በየሀገራቱ ከሚያገኟቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመጣመር፣ የተለያዩ ሥራዎችን ለየሀገሬው ሕዝብ በማቅረብ ድንበር የማይወስነው ወዳጅነት በመፍጠር፣ ጥበብን ለተሻለች ዓለም ለመፍጠር መንቀሳቀስ ነው፡፡

 

ቡድኑ ከኬፕታውን እስከ ካይሮ አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ኪሎ ሜትሮችን በመኪና በማቆራረጥና ለሁለት መቶ ተከታታይ ቀናት በመጓዝ ተልዕኮአቸውን የሚያሳካ ሲሆን፣ አባላቱ በሀገራቸው በቴአትር፣ በፊልም አዘገጃጀት፣ በሙዚቃ፣ በድምጻዊነት፣ በደራሲነትና በዳንስ ሙያ የሚታወቁ ናቸው፡፡ በየሙያ ዘርፋቸውም በየሄዱበት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፤ ከየሀገሬው ከያንያን ጋር በመሆን ሥዕል ይሥላሉ፤ አጫጭር ድራማዎችን ወይም ዘጋቢ ፊልሞችን ይሠራሉ፤ ሙዚቃዊ ተውኔቶችን ያቀነባብራሉ፤ ሙዚቃዎቻቸውን ከየሀገሩ ባህል ጋር አስማምተው ይከይናሉ፡፡

 

የዚህ ቡድን ተጓዦች በራሳቸው ተነሳሽነት እንጂ ወጪያቸው በመንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆነ ተቋማት የማይሸፈን ቢሆንም፣ ዩኔስኮና መሰል ተቋማት ዓላማቸውን ቁጥር ውስጥ በማስገባት፣ መጓጓዣ ይሆናቸው ዘንድ እገዛ አድርጎላቸዋል፡፡ የቡድኑ አባላት  ከአራቱም ክፍለ አህጉራት የተውጣጡ ናቸው፡፡ ከህንድ፣ ከጀርመን፣ ከአልጀርያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከኬንያና ከሌሎች  ሀገራት  ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ስምንት ሀገራት በመዞር በከፊል ዓላማቸውን አሳክተዋል፡፡

1

 

ተጓዦቹ ዘንድሮ ባደረጉት ጉዞ ጭብጥ አድርገው የተነሱት፣ በሰላም፣ በፍትህና በዐየር መዛባት ላይ ያተኮሩ ሥራዎችን ለመሥራት ሲሆን፣ ዘንድሮ ኢትዮጵያን አንዷ የጉዞአቸው መዳረሻ አድርገዋት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ/ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል የጉዞውን ዓላማ ግምት ውስጥ በማስገባት፣  ቡድኑ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ማረፊያና ማደርያ ቦታ እንዲያዘጋጅለት  የጠየቀውን ጥያቄ በመቀበል፣ አርቲስቶቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከማረፊያና ማደርያ ቦታ ውጪ፣ የመለማመጃ ቦታና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ምቹ አድርጎላቸዋል፡፡ አርቲስቶቹም አካዳሚው ያደረገላቸውን ትብብር በመግለጽ አክብሮታቸውን ለአካዳሚው ገልጸዋል፡፡

 

4

  

ሙያተኞቹ በቆይታቸው፣ (ማለትም ከጥር 15 እስከ  ጥር 29/ 2011 ዓ.ም) ለመካነ ኢየሱስ ትምሕርት ቤት የፊልምና የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዐውደ ጥናት በማዘጋጀት፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ትርኢት በማቅረብ (ናይሮቢ ከተማ ውስጥ የቀረጹትን በአየር መዛባት ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም በማሳየት፣ ሙዚቃዊ ድራማ አዘጋጅቶ በማቅረብና ሥዕሎችን ሠርቶ በማስረከብ) እና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሙዚቃ ትርኢቶችንና የልምድ ልውውጦችን በማድረግ  ከሙያው ቤተሰብና ከሙያው አድናቂዎች ጋር ተገናኝተዋል፡፡

2

 

ትርኢቶቹንም ከመሶብ ባህላዊ ባንድ፣ ከቴአትርና ዳንስ ተማሪዎች ጋር በመጣመር ሠርተው ለዕይታ አብቅተዋል፡፡

 

የ‹ግሬት አፍሪካን ካራቫን› ቡድን አባላት የመነሻ ጉዞአቸውን  ደቡብ አፍሪካ አድርገው፣ በዚህ ሳምንት መጀመርያ ደግሞ ወደ ሱዳን ያቀኑ ሲሆን፣ የሱዳን ቆይታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደግብጽ ያቀኑና የሁለት መቶ ተከታታይ ቀናት ጉዞአቸውን ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም፣ ጥበብ ድንበር አይወስናትም በሚል ዓላማ በየሀገራቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር የሠሩዋቸውን ኪናዊ ሥራዎች፣ ህንድ ሀገር በሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ታላቅ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ላይ አቅርበው እንደሚወዳደሩበት፣ አዘጋጆቹ አካዳሚው ባዘጋጀው መድረክ ላይ ጠቁመዋል፡፡

 


The Great African Caravan is the first major travel project by the Art Caravan Association. 12 international artists from all around the globe (India, Argentina, Britain, Uganda, Germany, and Kosovo) will travel for 7 month through the continent of Africa covering 12 countries. The adventurous journey will start in July 2018 in South Africa, go through South Africa, Mozambique, Zimbabwe, Zambia, Malawi,Tanzania, Rwanda, Uganda, Kenya, Ethiopia, and Sudan and end in Egypt in February 2019.
Throughout the journey, the artists will work with local humanitarian organisations, youth groups, and artists as well as further governmental bodies, cultural entities, and similar institutions to connect, strategise, design novel solutions for local challenges, and build awareness on SDGs with the broader aim of contributing to peace, global citizenship, and sustainable social change. In each country it will be collaboratively worked on a specific Sustainable Development Goals using art as a holistic, inspiring, and raising tool.
Workshops, dialogue creation, and art works will aim to raise awareness, offer sustainable tools for problem solving and peace building, and spread the spirit of interconnectedness, peace, and global citizenship. Individual projects as well as a documentary of the entire journey will additionally, each in their beautifully individual way, inspire, excite, and spread the mission of a better world. Furthermore it will provide material to bring awareness, spark discussions, and increase participation regarding significant topics such as migration, borders, peace, environment, and human rights.