‹‹ቁራኛዬ›› የተሰኘ የዶ/ር ሞገስ ታፈሰ ፊልም ውይይት ተደረገበት

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥር የሚገኘው የብላቴንጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ባሕላዊና ታሪካዊ ይዘት ያለው የዶ/ ሞገስ ታፈሰ ፊልም ‹‹ቁራኛዬ››  የካቲት 2/2011 ዓ.ም. ለኅብረተሰብ ዕይታ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡

ፊልሙ ከታየ በኋላ አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በፊልሙ ላይ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን ‹‹ፊልሙ ከአንድ ክፍለዘመን በላይ በምናብ ወደኋላ በመውሰድ የኢትዮጵያውያንን የፍትኅና የዕውነት ፍለጋ በተዋበ ቋንቋና ምስል ያሳየ ጥሩ የምርምር ሥራ ነው›› በማለት ገልጸውታል፡፡

1

በዚህ 46ኛው የጥበብ ውሎ መርሐ ግብር ላይ ላይ የፊልሙ አዘጋጅ / ሞገስ ታፈሰ በውይይቱ የተገኘ ሲሆን፣ ይኸን በቀደመው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና የስነ ልቦና ውቅር በወቅቱ የነበረውን ሥፍራ ለማሳየት የሚሞክረውን ፊልም የምርምር ሥራ እና ሌሎች ተግባራት ለመፈጸም ከአምስት ዓመት በላይ እንደፈጀባቸው ለታዳሚዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

በውይይቱ የአካዳሚው አባላት፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ፊልም ሠሪዎችና ሌሎች የጥበብ ቤተሰቦች ተሳትፈዋል፡፡