የኢትዮጵያ ግብርና ሜካናይዜሽን - እያዩ መራመድ


የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በየወሩ በሚያደርገው የሳይንሳዊ ገለፃና ውይይት መድረኩ ሐሙስ ኅዳር 27/2011 ዓ.ም ከ11፡00 ሠዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (5 ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ግቢ) የመሰብሰቢያ አዳራሽ 36ኛ መድረኩን የኢትዮጵያ ግብርና ሜካናይዜሽን - እያዩ መራመድ በተሰኘ ርዕስ በዶ/ር መለሰ ተመስገን የውይይት መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡

በመድረኩ:-

  • የኢትዮጵያ ሥነ ምኅዳራዊና ሶሺዮ-ኢኮኖሚያዊ ገፅታ፣
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ሂደትና ደረጃ፣
  • የሜካናይዜሽን ሥራ እዳይፋጠን የገደቡት ማነቆዎችና የሌሎች አገራት ልምድ እና
  • የኢትዮጵያን  የግብርና ዘርፍ ሥራ ከማዘመን እና የአርሶ አደሩን የምርት ሂደት ከማሻሻል አንፃር መደረግ ስለሚኖርባቸው ጉዳዮች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡
Date
End Date
Location
በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አዳራሽ (5 ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ግቢ)